Finot Academy Privacy
የግል መረጃ ጥበቃ (Privacy Policy)
Finot Academy የተማሪዎችን የግል መረጃ እና ደህንነት ለመጠበቅ የሚከተላቸውን መመሪያዎች ያንብቡ።
1. የምንሰበስበው መረጃ (Data We Collect)
በምዝገባ ወቅት የሚሰጡትን ሙሉ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ ጾታ እና የክፍያ ስክሪንሾት (Receipt) በደህንነት እንይዛለን።
2. የመረጃ አጠቃቀም (How We Use Information)
መረጃዎ የሚከፈሉት ኮርሶች መፈቀዳቸውን ለማረጋገጥ፣ ሰርተፊኬት ለማዘጋጀት እና አውቶማቲክ የኢሜይል ማሳወቂያዎችን ለመላክ ብቻ ያገለግላል።
3. የመረጃ ጥበቃ እና ሚስጥራዊነት (Data Security)
የተማሪዎች መረጃ ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ አይሰጥም። በቪዲዮዎች ላይ የሚታየው Dynamic Watermark የተማሪውን ስም፣ ስልክ እና Unique ID የያዘ ሆኖ የይዘት ስርቆትን ለመከላከል የሚንሳፈፍ ነው።
