Finot Academy Legal

የአገልግሎት ውሎች (Terms & Conditions)

እባክዎን የ Finot Academy መድረክን ከመጠቀምዎ በፊት የሚከተሉትን ህጎችና መመሪያዎች በጥንቃቄ ያንብቡ።

1. የአካውንት አጠቃቀም (Account Policy)

እያንዳንዱ የተማሪ አካውንት ለአንድ ሰው ብቻ የሚያገለግል ነው። አካውንትዎን ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት፣ ፓስወርድ ማጋራት ወይም በቡድን መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ነው።

2. የይዘት ጥበቃ እና የቅጅ መብት (Copyright & Security)

በ Finot Academy የሚቀርቡ የቪዲዮ ትምህርቶች፣ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች በሙሉ የ Finot Academy ንብረቶች ናቸው። ቪዲዮዎችን በሌላ ስልክ ማንሳት፣ በስክሪን ሪኮርደር መቅረጽ ወይም ማሰራጨት በህግ የሚያስጠይቅ ከመሆኑም በላይ አካውንትዎ ያለምንም ቅድመ ማሳወቂያ እንዲታገድ ያደርጋል።

3. የምዝገባ ክፍያ እና መጽደቅ (Enrollment & Refunds)

ተማሪዎች የሚልኩት የክፍያ ስክሪንሾት (Receipt) በአድሚን ከተረጋገጠ በኋላ ምዝገባው ይጸድቃል። የተሳሳተ ወይም ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ ማያያዝ ምዝገባው ውድቅ እንዲሆንና አካውንቱ እንዲታገድ ያደርጋል።